ቀጥታ፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም አስተዳዳሪ በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት ያደርጋሉ

አዲስ አበባ ታህሳስ 8/2011 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ዋና አስተዳዳሪ አቺም ስቴነር ከዛሬ ጀምሮ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ያደርጋሉ። ዋና አስተዳዳሪው በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከከፍተኛ የአገሪቱ መንግስት ባለልጣናት ጋር ተገናኝተው በልማት ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሏል። ከመንግስታቱ ድርጅት የተለያዩ አካላትና ሌሎች ቁልፍ የልማት አጋሮች ጋርም ይወያያሉ። አዲስ አበባ በሚከበረው የመንግስታቱ ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን 60ኛ ዓመት ምስረታ በዓል ላይም ይገኛሉ። የፕሮግራሙ ዋና አስተዳዳሪ በአዲስ አበባ ቦሌ ለሚ የሚገኘውን የኢንዱስትሪ ፓርክ የሚጎበኙ ሲሆን ከንግዱ ማህበረሰብ አባላት ጋርም ይወያያሉ። የልማት ፕሮግራሙ የኢትዮጵያ ቁልፍ ከሚባሉት የልማት አጋሮች መካከል ነው።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም