ኢትዮጵያ ስትመራው የነበረውን በአነስተኛ የእድገት ደረጃ የሚገኙ ሀገራት ቡድን ሊቀመንበርነትን ለቡታን አስረከበች

101
ታህሳስ 6/2011 ኢትዮጵያ ኤል ዲ ሲ በሚል ምህጻረ ቃል የሚታወቀውንና 47 በአነስተኛ የእድገት ደረጃ የሚገኙ ሀገራትን ቡድንን በሊቀመንበርነት ለተከታታይ 2 ዓመታት በመምራት ስትሰራ ቆይታለች፡፡ ከ1 ቢሊዮን ህዝብ በላይ የሚኖራቸውን 47 ሀገራት በመወከል ጠቃሚ የሆኑ የአየር ንብረት ለውጥ ድርድሮች በማድረግ የሀገራቱ ድምጽ በከፍተኛ ደረጃ እንዲሰማ የተሳካ ጥረት ማድረጓን የLDC ዋና ስራ አስኪያጁ የነበሩት አቶ ገብሩ ጀምበር ተናግረዋል፡፡ በአባል አገራቱ ስምምነት መሰረት የኢትዮጵያ የሊቀመንበርነት ጊዜ በመጠናቀቁ በደቡባዊ እስያ የባህር ዳርቻ ለምትገኘው ቡታን ከኢትዮጵያ አስረክባለች፡፡ ኢትዮጵያ ሊቀመንበር ሆና በሰራችባቸው ዓመታት ውጤታማ ስራዎች ማከናወኗ በርካታ የአባል ሀገራቱ ተወካዮች ምስጋና ሰጥተዋል፡፡ አዲስ ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት የቡታን ተወካይ  ሶናም ፊኒሾ ኢትዮጵያ በመሪነት ቆይታዋ የሀገራቱ ድምጽ በመሆን የማይተካ ሚና አበርክታለች፤ ምስጋና ይገባታል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ሀገራቸውም ከኢትዮጵያ ያገኘችውን ጠንካራ የመሪነት ልምድ በመጠቀም ለአረንጓዴ ልማት ሀገራቱን በመወከል ውጤታማ ስራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ቃል ገብተዋል፡፡ የኢትዮጵያ የአካባቢ፣የደንና አየር ንብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ፈቃዱ በየነም ለአዲሱ ፕሮዚደንት መልካም የስራ ዘምን እንዲሆንላቸው በመመኘት ለሀገራቱ አንድነትና ብልጽግና መጠናከር አብረን እንሰራለን ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም