ምክር ቤቱ በቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ዜና እረፍት የተሰማውን ሐዘን ገለጸ - ኢዜአ አማርኛ
ምክር ቤቱ በቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ዜና እረፍት የተሰማውን ሐዘን ገለጸ
አዲስ አበባ ታህሳስ 6/2011 የፌዴሬሽን ምክር ቤት በቀድሞው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ዜና እረፍት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ። የቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ታህሳስ 19 ቀን 1917 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተወለዱ ሲሆን በተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊነቶች አገራቸውንና ህዝባቸውን አገልግለዋል። ምክር ቤቱ ባወጣው የሐዘን መግለጫ ፕሬዚዳንት ግርማ ለ12 ዓመታት የአገሪቱ ርዕሰ ብሄር በነበሩበት ወቅት ለህገ-መንግስቱ ታማኝ በመሆንና የተጣለባቸው ኃላፊነት በመወጣት የኢትዮጵያን ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ አገልግለዋል ብሏል።በቀድሞው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ኃዘን በመግለጽም ለቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጆቻቸውና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን ተመኝቷል።