በስደት ላይ ሆነው ኢትዮጵያዊነታቸውን የሚገልጽ ሰነድ ላልነበራቸው ዜጎች ፓስፖርት እየተሰጠ ነው

102
አዲስ አበባ ታህሳስ 4/2011 በህገ ወጥ መንገድ ከአገር ተሰደው ኢትዮጵያዊነታቸውን የሚያሳይ ሰነድ ስላልነበራቸው ''አገር አልባ'' ሆነው የቆዩ ዜጎች ፓስፖርት እየተሰጣቸው ነው ተባለ።  በተለያየ ምክንያት መኖሪያቸውን ኢትዮጵያ ያደረጉ የተለያዩ አገራት ዜጎች ቋሚ የመኖሪያ ፍቃድ እንደተሰጣቸውም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።  የሚኒስቴሩ ቃለ አቀባይ አቶ መለስ አለም በዛሬ መግለጫቸው እንዳሉት በውጭ የሚኖሩ ዜጎችን ደህንነት ከማስጠበቅና ወደ እነሱም የቀረበ የቆስላ አገልግሎት ከመስጠት አንጻር የተሳካ ስራ እየተሰራ ነው።  ከሰሞኑ በተለያዩ ምክንያቶች በሳዑዲ መንግስት ቁጥጥር ስር ውለው የቆዩ ኢትዮጵያዊያን እስረኞች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እየተደረገ ያለውን ጥረት ለአብነት ጠቅሰዋል። እስካሁንም 2 ሺህ 250 ዜጎች ከእስር ቤት ተፈተው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ሁኔታዎች መመቻቸታቸውንና በስራ ላይ በነበሩ ጊዜ ያልተከፈላቸው ደመወዝም በመንግስት ድርድር እንዲከፈላቸው መደረጉን አንስተዋል። በዚህም ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ክፍያ እንዲፈጸምላቸው ተደርጓል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም