ቀጥታ፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ከሁለት ዓመት በፊት ኃይል ማመንጨት አይጀምርም

አዲስ አበባ  ታህሳስ  4/2011 የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ ኃይል ማመንጫ ከሁለት ዓመት በፊት ማመንጨት እንደማይጀምር ተገለጸ። ግድቡ እንደቆመ የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ መሆኑንና ግንባታው ለደቂቃም ሳይቋረጥ 'በመካሄድ ላይ ነው' ተብሏል። የውሃ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጀነር ስለሺ በቀለ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብርሃም በላይና የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮን ያሳተፈና በግድቡ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል። ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት ግድቡ የመጀመሪያ ምዕራፍ ኃይል ለማመንጨት ከዚህ በኋላ ሁለት ዓመት ይወስድበታል። ይህ የሆነው በብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሲሰራ የነበረው የሃይድሮ ኤሌክትሪካል ስራ በታቀደለት ጊዜ ባለመከወኑ ነው ብለዋል። ግንባታው እንደተቋረጠ የሚወራው ወሬ ከእውነት የራቀ መሆኑን ገልጸው አጠቃላይ ግንባታው በፈረንጆቹ አቆጣጠር 2022 እንደሚጠናቀቅ አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም