ቀጥታ፡

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ ህብረተሰቡ ለሰላምና የህግ የበላይነት ዘብ መቆም አለበት-ፕሬዝዳንት ለማ መገርሳ

ጅማ ህዳር 29/2011 በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ ህብረተሰቡ ለሰላምና የህግ የበላይነት ዘብ መቆም እንዳለበት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ ተናገሩ። ፕሬዝዳንቱ እንዳሉት የኢንዱትሪ ፓርኩ ለአካባቢው ነዋሪዎች የስራ ዕድል ከመፍጠር በላይ የክልሉ ኢንቨስትመንትን የሚያነቃቃ ነው። ፓርኩ ለዩኒቨርሲቲዎች ለምርምርና ሰርቶ ማሳያዎች ማዕከል በመሆን ለኢንዱስትሪዎች መስፋፋት የጎላ ሚና ይኖረዋልም ብለዋል። ክልሉ እምቅ የተፈጥሮ ሀብት እና የአገልጋይነት ስሜት ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ያሉበት በመሆኑም ለኢንቨስትመንትና ለውጪ ባለሀብቶች የተመቸ መሆኑን ገልጸዋል አቶ ለማ። ይሁን እንጂ በክልሉም ሆነ በአገሪቷ የውጪ ባለሀብቶችን በኢንቨስትመንትና በልዩልዩ እንዲስዱስትሪ ለመሳብ ሰላምና ደህንነት መጠበቅ አለበት፤ በቂ ግበዓትና የሰው ኃይል ከማቅረብ ባለፈም ህብረተሰቡ ለሰላም ዘብ መቆም ይኖርበታል ብለዋል። ዕድገት ሊመጣ የሚችለው የህግ የባላይነት ሲከበር፣ ሰላም ሲሰፍንና ለዜጎች የአገልጋይነት መንፈስ ሲጎለብት መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ የክልሉ ሰላምና ዕድገት እንዲሁም የህገ የበላይነት እንዲረጋገጥ ቅድሚያ መስጠት ይኖርበታል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ ከሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽርና ከጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ ጋር በጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ምርቃት ላይ ተገኝቷል።                            
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም