ቀጥታ፡

የአለም ባንክ በፈረንጆቹ 2018 ለኢትዮጵያ የሰጠው ብድርና ድጋፍ 3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ደርሷል

አዲስ አበባ ህዳር 28/2011 የአለም ባንክ ቡድንና አጋርነት እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር በ2018 ለኢትዮጵያ የተለያዩ ልማት ስራዎች ያደረገው ድጋፍና የብድር መጠን 3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር መድረሱን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ። የአለም ባንክ ቡድን ለአገሪቱ እያደረገ ያለው ድጋፍና ብድር ለመሰረተ ልማት ግንባታዎች፣ የሰው ኃይል ለማብቃት፣ ለቴክኖሎጂና ለተለያዩ ልማቶች ማስፋፊያ እንዲሁም ለልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች ነው። የዓለም ባንክ በዓለም ላይ የሚታየውን አስከፊ ድህነት ለመቀነስ፣ የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻልና የአገሮች የልማት አጀንዳዎችን ለመደገፍ ይሰራል። በተያዘው ዓመትም የአለም ባንክ ቡድንና አጋርነት ከሶስት ቢሊዮን ብር በላይ ለኢትዮጵያ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ ድጋፍና ብድር መስጠቱን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያሳያል። እአአ በ2017 ባንኩ 965 ሚሊዮን ብር በ2016 1 ነጥብ 753  ቢሊዮን ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን የዘንድሮ ዓመት ከሌሎች ዓመታት ይልቃል። ባንኩ ከንጉሱ ጀምሮ ድጋፍ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ኢትዮጵያም በተለይ እአአ ከ1980 ዎቹ ጀምሮ ለልማት አመቺ የሆነ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ፖሊሲዎችን በመቅረጽ ከእርዳታ እንዲሁም ከወለድ ነጻና በረጅም ጊዜ የሚከፈል ብድር ተጠቃሚ ስትሆን ቆይታለች። የአለም ባንክ ዳይሬክተር ሚስ ካሮሊን ተርክ ዛሬ የተደረገውን የ2 ነጥብ 753 ቢሊዮን ብር የብድር ሰምምነት ሲካሄድ እንዳሉት፤ ባንኩ ለኢትዮጵያ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም