ውልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በሜዳው ደቡብ ፖሊስን አንድ ለባዶ አሸነፈ

36
መቀሌ ህዳር 22/2011 ዛሬ በተካሄዳው የኢትዮጰያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ደቡብ ፖሊስን አንድ ለባዶ አሸነፈ። በመቀሌ ከተማ ትግራይ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ በሁለቱ ቡድኖች መካከል ተመጣጣኝ ፉክክር የታየ ቢሆንም ከእረፍት በፊት የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በአጥቂው ኤፍሬም አሻሞ አማካይነት ባስቆጠረው ግብ አሸናፊ ሆኖ ወጥቷል። ከእረፍት በኋላ ብዙ የግብ ሙከራ ባይታይም በሁለቱም ቡድኖች መካከል ጨዋታው ቀዝቃዛ ነበር። “የደቡብ ፖሊስ አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ጥሩ የተጫወትን ቢሆንም የነበሩብን ክፍተቶች ተሸንፈን እንድንወጣ አድርገውናል” ብለዋል። በስታዲየሙ የነበረው የተመልካች ድጋፍ ጨዋነት የተሞላበት እንደነበረው አሰልጣኙ ገልጸዋል። የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ አሰልጣኝ ፀጋይ ኪዳነማሪያም በሰጡት አስተያየት “ከተከታታይ ሽንፈት በኋላ ወደ አሸናፊነት በመመለሳችን ጥሩ ተጫውተን ጥሩ ተፎካካሪ እንሆናለን” ብለዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም