የኦዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ በአገሪቷ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ነው

53
አዲስ አበባ ህዳር 20/2011 የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኦዴፓ/ ማዕከላዊ ኮሚቴ በአገሪቷና በኦሮሚያ ክልል ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ነው። የድርጀቱ የገጠር አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ እንዳስታወቁት ማዕከላዊ ኮሚቴው በመላው አገሪቷም ሆነ በክልሉ አስተማማኝ ሰላምና ማረጋጋት ማስፈን በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት ላይ ናቸው። የህግ የበላይነትን ለማስከበር የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉበት ሁኔታዎች ላይም ምክክር ተደርጎ አቅጣጫ ይቀመጣል ብለዋል። የዴሞክራሲ ምህዳርንም ማስፋትና ሌሎች ጉዳዮችም በምክክሩ እንደሚዳሰሱ ነው መረጃው የሚያመላክተው።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም