ቀጥታ፡

ዶክተር ወርቅነህ ከአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ቲቦር ናጊ ጋር እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ ህዳር 20/2011 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ቲቦር ናጊ ጋር እየተወያዩ ነው። ለሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ትናንትና አዲስ አበባ የገቡት ቲቦር ናጊ በአሁኑ ወቅት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋር እየመከሩ ይገኛል። ዶክተር ወርቅነህ ከረዳት ሚኒስትሩ ጋር በሁለትዮሽ፣ በቀጣናዊና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል። ረዳት ሚኒስትሩ በስድስተኛው የአሜሪካ-አፍሪካ ህብረት የከፍተኛ አመራሮች ውይይት ላይ ተሳትፈዋል። ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ጋር ተገናኝተውም መክረዋል። የቀድሞ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ቲቦር ናጊ የኢትዮጵያ ጉብኝት ከአዲሱ ሹመታቸው በኋላ የመጀመሪያ ነው። አሜሪካ በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የኢኮኖሚና ዲሞክራሲ ለውጥ እንደምትደግፍና የአፍሪካ ኀብረት በአጀንዳ 2063 ያቀደውን ከግብ ለማድረስ ድጋፏን እንደምትቀጥልም ተገልጿል። ቲቦር ናጊ እ.አ.አ ከ1999 እስከ 2002 ድረስ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉ ናቸው።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም