የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጣና ሐይቅ ላይ የተከሰተውን እምቦጭ አረም ለማስወገድ የ10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጣና ሐይቅ ላይ የተከሰተውን እምቦጭ አረም ለማስወገድ የ10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

ባህር ዳር ህዳር 16/2011 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጣና ሐይቅ ላይ የተከሰተውን እምቦጭ አረም ለማስወገድ የሚያግዝ የ10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ዛሬ ከባህር ዳር ከተማ ወጣቶችና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት የከተማ አስተዳደሩ ያደረገውን ድጋፍ አበርክተዋል፡፡ በእዚህ ወቅት ከንቲባው ጣናን መታደግ የውለታ ጉዳይ ሳይሆን የግዴታ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል። ድጋፉን ቀጣይ ለማድረግ በአዲስ አበባ ሕብረተሰቡን የማነቃነቅ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክተዋል። በኢንጅነር ታከለ ኡማ የተመራውና ከ300 በላይ የአዲስ አበባ ወጣችን የያዘው የልዑካን ቡድን ትናንት በጣና ሐይቅ የእምቦጭ አረም ነቀላ ሥራ ማከናወኑ ይታወሳል። የገንዘብ ድጋፉን የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምግባሩ ከበደ ከኢንጂነር ታከለ ኡማ ተረክበዋል።