ቀጥታ፡

በኢትዮጵያ ባለፉት 13 ቀናት ሲሰጥ የቆየው ዓለም አቀፍ የዊልቸር ቅርጫት ኳስ ስልጠና ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ህዳር 15/2011 በአዲስ አበባ ባለፊት 13 ቀናት ሲሰጥ የቆየው ዓለም አቀፍ የዊልቸር ቅርጫት ኳስ ስልጠና ዛሬ ተጠናቀቀ። ስልጠናው የተሰጠው ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማህበር ከኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ነው። በስልጠናው የተካፈሉት በአገሪቱ የተለያዩ  የቅርጫት ኳስ ስልጠና ጣቢያ ፕሮጀክቶች የሚገኙና  ከዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ናቸው። በተጨማሪም ከሱዳን፣ ዩጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ከዲሞክራቲክ ኮንጎ ሌሎች የአፍሪካ አገራት የመጡ ሰልጣኞችም መካፈላቸውን የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ይመር ሃይሌ ገልፀዋል። ስልጠናው የተሰጠው ደግሞ ከአሜሪካ ፣ ከቱርክና ከደቡብ አፍሪካ በመጡ ባለሙያዎች ሲሆኑ ስልጠናው ዳኞችን፣ አሰልጣኞችንና ተጫዎቾችን ያካተተ ነበር። በዚህ ስልጠና በዳኝነት የተካፈሉ ሰልጣኞች የተግባርና የጽሁፍ ፈተና የወሰዱ ሲሆን ፈተናውን ካለፉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመዳኘት እድል ያገኛሉ ተብሏል። ከህዳር 4 ቀን 2011 ጀምሮ ለ13 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው ይህ ስልጠና የአካል ጉዳት ልየታንም ያካተተ ነበር።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም