ቀጥታ፡

የሰብዓዊ መብት ተቋማት የፖሊሲ ፎረም ዓለም ዓቀፍ ጉባዔ ነገ በአዲስ አበባ ይጀምራል

አዲስ አበባ ህዳር 13/2011 የሰብዓዊ መብት ተቋማት 2ኛው የፖሊሲ ፎረም ዓለም ዓቀፍ ጉባዔ ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ጉባዔው በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ በአፍሪካ ብሔራዊ የሰብአዊ መብት ተቋማት ትስስር፣ በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የፖለቲካ ጉዳዮች ዲፓርትመንትና በአፍሪካ የፀረ-ሙስና አማካሪ ቦርድ ትብብር የሚካሄድ ነው። ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ጉባዔ ከ180 በላይ ዓለም ዓቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማት ኮሚሽነሮችና የዴሞክራሲ ተቋማት ኃላፊዎች እንደሚገኙበት ይጠበቃል። ጉባኤው የአፍሪካ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ባሉበት ደረጃ፣ በአህጉር ደረጃ ሙስናን ከመዋጋት አንፃር ባላቸው ሚና እንዲሁም መልካም አስተዳደር፣ ሰብዓዊ መብቶችን ማክበር፣ ፍትህና የህግ የበላይነት በሚሉ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል። በዚህ ጉባኤ ከ44 የአፍሪካ አገሮች የተውጣጡ አባላት እንደሚሳተፉበት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ ማርሴ አሰፋ ለኢዜአ ገልጸዋል።                                  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም