ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ እጩ ሆነው ቀረቡ - ኢዜአ አማርኛ
ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ እጩ ሆነው ቀረቡ
ህዳር 13/2011 ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ እንዲሆኑ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በእጩነት ቀርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተወካዮች ምክር ቤት አባላት እንዳብራሩት እጩዋ በገለልተኝነት ቦርዱን እንደሚመሩ ታምኖባቸዋል። ወ/ሪት ብርቱካን ለመንግስትም ቢሆን እጅ የማይሰጡ፤ ለዚህም ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ የሆኑ እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያምንበትን ተቋም ይመራሉ ነው ያሉት፡፡