አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን ከአሜሪካው ቦይንግ ኩባንያና ከሲያትል አጋር ድርጅት ስራ አስፈጻሚዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ  ህዳር 12/2011 በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን ከአሜሪካው ቦይንግ ኩባንያና ከሲያትል አጋር ድርጅት ስራ አስፈጻሚዎች ጋር ተወያዩ። አምባሳደር ካሳ የኢትዮጵያና የአሜሪካን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ከድርጅቶቹ የስራ ሃላፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት አካሂደዋል። በአሜሪካ ሲያትል የኢትዮጵያን ቢዝነስ ምክር ቤት ለማቋቋም ቦይንግ ኩባንያና የታላቋ ሲያትል አጋር ድርጅት ድጋፍ እንዲያደርጉ ስምምነት መደረሱን የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል። የሲያትል አጋር ድርጅት በአሜሪካ ሲያትል ያለውን የኢኮኖሚ እድገት ለማሳደግ የተቋቋመ የመንግስትና የግል የጋራ ድርጅት ነው። ቦይንግ ኩባንያም 787 ድሪም ላይነር እና ቦይንግ 777ን ጨምሮ የተለያዩ ዘመናዊ አውሮፕላኖችን በማምረትና ለዓለም ገበያ በማቅረብ ቀዳሚ መሆኑ ይታወቃል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም