ቀጥታ፡

የመውሊድ በዓል በታላቁ አንዋር መስጅድ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ ህዳር 11/2011 1 ሺህ 493ኛው የነብዩ መሀመድ የመውሊድ በዓል በእምነቱ ተከታዮች በታላቁ አንዋር መስጅድ እየተከበረ ነው። በበዓሉ መክፈቻ ላይ ቁርአን የተቀራ ሲሆን በታዳጊ ተማሪዎች ነሺዳ ቀርቧል። የነብዩ መሐመድ የህይወት ታሪክና ያከናወኗቸውን ተግባራት የተመለከተ ትምህርት በሃይማኖት አባቶች የሚሰጥ ሲሆን መንዙማና ዱአ /ፀሎት/ በበዓሉ አከባበር የሚከናወኑ ተግባራት ናቸው።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም