ኢትዮጵያና ግብጽ በመተማመንና በመተባበር መስራት አንዳለባቸው ተገለፀ

121
አዲስ አበባ ህዳር 9/2011 ኢትዮጵያና ግብጽ በመተማመንና በመተባበር በመስራት የህዝቦቻቸውን የላቀ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባቸው ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከግብጽ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ ማድቦሊ ጋር ከህብረቱ ስብሰባ ጎን ለጎን ዛሬ ተወያይተዋል፡፡ በዚሁ ወቅት ኢትዮጵያ፣ በግብጽና በሱዳን መካከል የሚካሄደው የሶስትዮሽ የቴክኒክ ምክክር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለማድረግም መሪዎቹ ተስማምተዋል፡፡ በኢትዮጵያና ግብጽ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነትን በተለይም የጋራ ትብብርን ማጠናከር በሚቻልበት መንገድ ላይም መሪዎቹ መክረዋል። ኢትዮጵያና ግብጽ እንደ አገር በመሪዎች ደረጃም እንዲሁ መልካም ግንኙነት ያላቸው መሆኑን መናገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ ፅህፈት ቤት ለኢዜአ ገልጿል።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም