ለ11ኛው የአፍሪካ ህብረት ልዩ የመሪዎች ስብሰባ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት መሪዎች አዲስ አበባ እየገቡ ነው

121
አዲስ አበባ ህዳር 7/2011 ለ11ኛው የአፍሪካ ህብረት ልዩ የመሪዎች ስብሰባ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት መሪዎች አዲስ አበባ እየገቡ ነው፡፡ ነገና ከነገ ወዲያ ለሚካሄደው 11ኛው ልዩ የመሪዎቹ ጉባዔ የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር ሐሰን አልበሽር፣ የጅቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማርጌሌ እና የዝምባቡዌው ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ሚናንጋጉዋ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰዋል። በተመሳሳይ የሶማሊያው ምክትል ፕሬዝዳንት፣ የቻድ ሪፓብሊክ ፕሬዝዳንት እድሪስ ዲቤ፣ እንዲሁም የናሚቢያው ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሃጌ ጌይንጎብ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰዋል። እንዲሁም  የአልጄሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር አህመድ ኦያሂያ፣ እና የኒጀርር ፕሬዝዳንት መሐመዱ ኢሶፉ አዲስ አበባ ገብተዋል። የአገራቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉባዔ ከህዳር 5 ቀን 2011ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ መቆየቱ ይታወሳል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም