ቀጥታ፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በክብር ቆንስል ኤሊያስ ሳቦሪ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ

አዲስ አበባ ህዳር 7/2011 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በፊንላንድ የኢትዮጵያ የክብር ቆንስል ኤሊያስ ሳቦሪ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለጹ። "ኤልያስ ሳቦሬ የኢትዮ-ፊንላንድ ወዳጅነት እንዲጠናከር አስተዋጽኦ አበርክተዋል" ያሉት ዶክር ወርቅነህ የአገሪቷን የቱሪስት መስህብ፣ ንግድና ኢንቨስትመንት በማስተዋወቅ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ እንዲጠናከር ማድረጋቸውን አውስተዋል። ኤልያስ ሳቦሬ እ.ኤ.አ. ከ2004 ጀምሮ በፊንላንድ የኢትዮጵያ የክብር ቆንስል በመሆን ለኢትዮጵያና በዚያ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጥቅም መጠበቅ ያላሰለሰ ጥረት ማድረጋቸውንም አንስተዋል። በክብር ቆንስል ኤሊያስ ሳቦሪ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን በመግለጽም ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጸህፈት ቤት ለኢዜአ አስታውቋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም