ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አስተዳደር በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን ተጠየቀ

አዲስ አበባ ህዳር 6/2011 በኢትዮጵያ የተዘረጋው የፌዴራል ፖለቲካ ስርዓት ሁሉንም ዜጋ በእኩልነት ተጠቃሚ ሊያደርግ በሚያስችል መንገድ በአግባቡ ተግባራዊ መሆን እንዳለበት ተገለፀ። በአዲስ አበባ የሚካሄደውን 13ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ "ፌዴራሊዝም ሥርዓት ትሩፋቶችና ስጋቶች" ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ዛሬ ተካሂዷል። የከተማ አስተዳደሩ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ከአዲስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው በዚሁ ፓናል ውይይት ላይ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርዎችና የዘርፉ ምሁራን ተሳትፈዋል። ተወያዩቹ እንደሚሉት በዓለም ካሉ አገራት መካከል 40 በመቶዎቹ የተለያየ መለክ ያለው ፌዴራል ሥርአት ተከታዩች ናቸው፤ በአግባቡ የስርአቱን መርሕ ተጠቅመው ለማስኬድ በመቻላቸው ለውጥ አምጥተውበታል። በኢትዮጵያ ተግባራዊ የተደረገው የፌዴራል ፖለቲካ ስርዓትም ሳይንሳዊ በሆነና በጥናት ላይ ተመስርቶ የሚተገበር ከሆነ በራሱ የግጭት መንስኤ ሊሆን እንደማይችል ነው በውይይቱ ወቅት የተገለፀው። በመሆኑም የፌዴራል ስርዓቱ መላውን ዜጋ  ተጠቃሚ ሊያደርግ በሚያስችል አግባብ ተግባራዊ የሚሆንበት መንገድ መቀየስ አለበት ተብሏል። በውይይቱ ላይ እንደተገለፀው የኢትዮጵያ ፌዴራል ስርአት መሰረት የሆነው የክልሎች አደረጃጀት በጥናት ላይ ያልተመሰረተ፤ በአግባቡ ባለሙያዎች ያልተሳተፉበት ነው። ምንም እንኳ ስርዓቱ በተለይ ከማንነት ጋር በተያያዘ የተለያዩ ፈተናዎች እየገጠሙት ቢሆንም ብሔር ብሔረሰቦች እራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ እድል መስጠቱ፤ ህዝቡም እኩልነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል  ሕገ-መንግስት ባለቤት መሆኑ በመልካም ትሩፋት የሚታይ መሆኑም ተመልክቷል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌደራሊዝምና የሰብአዊ መብት ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ መንግስቱ እንደሚሉት በአሁኑ ወቅት ያለው የክልሎች አደረጃጀት በጥናት የተመሰረተ አይደለም ይላሉ። “መልካም ነገሮቹ እንደተጠበቁ ሆነው ጉድለቶቹን አንስተን ብናይ ለመሻሻል ለወደፊቱ ለማስተካከል እድል ይሰጣል፡፡ አንዱ ችግሩ የሚጀምረው የፌዴራል ስርአቱን የመሰረቱት ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ናቸው ይላል ልክ የተለያየ ቆይተው እንደገና ተነጋግረው ተስማምተው ወደ አንድ እንደመጡ፡፡ እኛ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ብሎ ይጀምራል እኛ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ብሎ አይደለም አይጀምርም ይሔ ከሌሎች የሚለይበት አንዱ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የክልሎች አደረጃጀት በሽግግር ወቅት ነው የተሰራው ።ይሔ አደረጃጀት በጥናት ላይ የተመሰረተና የተሟላ አልነበረም የተለያየ ባለሙያዎችን ያሳተፈ የፖለቲካ ድርጅቶች በተለይ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጆች ሐሳባቸውነ በብቃት እንዲሰጡትበት አልተደረገም። ከአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር/ኢህአዴግ/ አቶ ቢኒያም አደራ በበኩላቸው  የኢትዮጵያ ዲሞግራፊ  እውነታ አሁን ላይ ሆነን ስናየውና ከዛሬ 27 ዓመት በፊትያለውን ስናየው የፌዴራል ስርአት አማራጭ ነበር ወይስ ግዴታ የሚለውን ልናይ እንችላለን። የቀድሞ የተፈካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አባል አቶ ሙሼ ሰሙ “ለኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም ወሳኝ አጀንዳ ነው ።ምክንያቱም ኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም መሰረታዊ ነገሩ የሕዝቦችን ተጠቃሚንት ማረጋገጥ ነው አንዱ ለአስተዳደር አመቺነትን ማምጣት ለልማት አመቺነትን ማእከል አድርጎ መንቀሳቀስ ፣ፍትሕን በቅርብ ርቀት የሚያገኝቡትን ሁኔታ ማመቻቸት፣በራሳቸው ሪሶስርስ አካባቢያቸው ሀብት ተጠቃሚ እንዱሆኑ ማድረግ ቋቋቸውነ ባሕላቸውን ማንነታቸው እንዲዳብሩና በቋንቋቸው በባሕላቸው እንዲዳኙ እንዲማሩ ማድረግን ሕዝብን የመድረስ ጥያቄ ነው ፌዴራሊዝም ስለዚህ  ከፌዴራሊዝም ጋር ጠብ ሊኖር አይችልም ግን ምን አይነት ፌዴራሊዝም እንገባ የሚለው ነው መሰረታዊ ጥያቄ ሆኖ የሚመጣው። ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/የፖለቲካ ፓርቲ ዋና ዳየሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ከዚህ በፊት የነበረው ሲስተም  በኢትዮጵያዊነት በለው በፌውዳል ሲስተም በሉት ለሕዝቡ አይመችም ጥሩ አልነበረም። ብሔረተኝነትም ደግማ ለሕዝቡ አይመችም ጥሩ አይደለም  እነዚህ ሁለቱ ነገሮች፤አሁን እኛ የምንፈልገው ሰው በሰውነቱ በቂ ነው የኔን መብት ለመጠበቅ የኔን ብሔርና ቀለም የተወለዱኩበን ተውትና ሰው በመሆኔ ብቻ በቂ ነው፤የኦሮሞ መብት ለመጠበቅ ሰው በመሆኑ ብቻ ይበቃል ፣የትገሬ መብት ለመጠበቅ ሰው በመሆኑ ብቻ ይበቃል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም