ሳጅን ኪዳኔ አሰፋ እና ሳሙኤል ግዲሳ የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ

115
አዲስ አበባ ህዳር 6/2011 ሳጅን ኪዳኔ አሰፋ እና ሳሙኤል ግዲሳ የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ። ዋና ሳጅን አሰፋ ከሌሎች የደህንት ሰዎች ጋር በመሆን በሽብርተኝነት ተጠርጥረው የሚያዙ ግለሰቦችን በማሰቃየት የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸማቸው ተገልጿል። ሌላኛው ተጠርጣሪም ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ባሻገር በህገ-ወጥ መንገድ ሃብት ለማካበት ሰበታ ላይ ኃላፊዎችን አስፈራርተዋል በሽብር እንዲታሰሩም አድርገዋል ተብሏል። ተጠርጣሪዎችን አፍኖ በመያዝም በስውር እስር ቤት ለአምስት ወራት ለፍርድ ሳይቀርቡ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል። ፖሊስ ሰብዓዊ መብት ጥሰት የደረሰባቸው ሰዎች የአካልና የስነልቦና ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ያስፈራሯቸዋል፣ ሌሎችንም ተጠርጣሪዎች ለመያዝም የጠየቁት ዋስትና ውድቅ ይደረግ ብሏል። በመሆኑም ዜጎችን በማሰቃየትና በሽብር ወንጀል በማስፈራራት ተገቢ ያልሆነ ገንዘብ ተቀብለዋል፣ ሃብት አካብተዋል በሚል መጠርጠራቸውንና በስቃይ ላይ የነበሩና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ስላሉ የቤተሰብ ቃል ለመቀበል የ14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ጠይቋል። የተጠርጣሪዎቹ ተከላከይ ጠበቆች ቀጠሮ አያስፈልግም በሚል የዋስትና መብት ቢጠይቁም ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ ፖሊስ የጠየቀውን የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ለህዳር 20 ቀን 2011 ዓም ቀጠሮ ሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም