በመስቃን ወረዳ የተከሰተው ግጭት ጉዳት አደረሰ

64
ሀዋሳ ህዳር 5/2011 በጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ ዛሬ በተከሰተ ግጭት የአስር ሰዎች ህይወት ማለፉንና ለጊዜው ብዛታቸው ባልተለየ ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ መድረሱን የዞኑ ፖሊስ አስታወቀ። የዞኑ ፖሊስ ኃላፊ ኮማንደር ውድማጣስ አወል ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ችግሩ የተከሰተው በመስቃን ወረዳ ኢንሴኖ ከተማ ውስጥ ነው። ዛሬ ጠዋት ረፋድ ላይ በከተማው በተከሰተው በዚህ ግጭት ከሞቱትና ከቆሰሉት በተጨማሪ በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውንም ኃላፊው ገልጸዋል። የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት፣የፌዴራል ፖሊስና የክልሉ ልዩ ኃይል ሁኔታውን ለመቆጣጠር ባደረጉት ጥረት አሁን ላይ አካባቢው ወደ መረጋጋት መመለሱን ኮማንደር ውድማጣስ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም