የኢትዮጵያ የኦሎፒክ ቢሄራዊ ቡድን የሱማሌ አቻውን በሰፊ የጎል ልዩነት አሸነፈ

68
ህዳር 5/2011 ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው የቅድመ ማጣሪያ የአፍሪካ ዞን የኦሎፒክ  ጫወታ  የኢትዮጵያ ከ23 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን የሱማሊያ አቻውን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ጎል ነው ያሸነፈው፡፡ በጃፓን ቶክዮ ከሁለት አመት ብኋላ ለሚደረገው የእግር ኳስ ጫወታ ለመሳተፍ በሚካሄደው ማጣሪያ ጫወታ ነው ድል የቀናው፡፡ ለኢትዮጵያ ቡድን  ጎሎቹን እስራኤል እሼቱ፣ ከነዓን ማርክህ፣ አማኑኤል ገ/ሚካኤልና አቡበከር ሳኒ በፍጹም ቅጣት ምትና በጫወታ  አስቆጥረዋል፡፡ በጨዋታው አቡበከር ሳኒ  በሱማሊያው መሓመድ አብዱልቃድር  ላይ በሰራው ጥፋት በቀይ ካርድ ከሜዳው ተሰናብቷል፡፡ የኢትዮጵያ ከ23 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን የመልስ ጫወታውን ከሱማሊያ አቻው ጋር በጅቡቲ ህዳር 11 /2011 ያደርጋል፡፡ ቡድኑ የደርሶ መልስ ውድድሩን ካሸነፈ ከማሊ ብሄራዊ ቡድን ጋር የሚያደርግ ይሆናል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም