ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ በቁጥጥር ስር የዋሉ የሙስና ወንጀል ተጠርጣሪዎችን ይፋ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ በቁጥጥር ስር የዋሉ የሙስና ወንጀል ተጠርጣሪዎችን ይፋ አደረገ
100
አዲስ አበባ ህዳር 4/2011 የፌዴራሉ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦችን ዝርዝር ይፋ አደረገ።
- ብርጋዴር ጄኔራል ጠና ቁርንዴ ኢጄታ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የማርኬቲንግ ኃላፊ
- ብርጋዴር ጄኔራል ብርሃ በየነ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የኮርፖሬት ኦዲትና ኢንስፔክሽን ኃላፊ
- ብርጋዴር ጄኔራል ጥጋቡ ፈትላ መረሳ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የኮርፖሬት ሎጂስቲክስና ሰፕላይ ኃላፊ
- ብርጋዴር ጀኔራል ሃድጉ ገብረጊወርጊስ ገብረስላሴ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የኮርፖሬት ኒው ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ኃላፊ
- ኮሎኔል ሸጋው ሙሉጌታ ተስፋሁን - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የወታደራዊ ምርቶች ኦፕሬሽን ኃላፊ
- ኮሎኔል ሙሉ ወልደገብርዔል ገብረእግዛብሄር - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የኒው ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ኃላፊ የነበሩ
- ኮሎኔል ዙፋን በርሄ ይህደግላ - የመከላከያ ጤና ኮሌጅ ሰራተኛ
- ሌተናል ኮሎኔል አስምረት ኪዳኔ አብርሃ - የጋፋት አርማመንት ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ተወካይ ኃላፊ የነበሩ
- ኮሎኔል አለሙ ሽመልስ ብርሃን - በብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን በኮርፖሬት ሎጂስቲክስና ሰፕላይ የትራንስፖርት ኃላፊ
- ኮሎኔል ያሬድ ሃይሉ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በኮርፖሬት ኒው ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት የፕሮጀክት ኃላፊ
- ኮሎኔል ተከስተ ሀይለማሪያም አድሃኑ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የኒው ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ኃላፊ የነበሩ
- ኮሎኔል አዜብ ታደሰ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በኮርፖሬት ማርኬቲንግ የሽያጭ ኃላፊ
- ሻለቃ ሰመረ ሀይሌ ሀጎስ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በደጀን አቪዬሽን የኢንዱስትሪ ኦፕሬሽን ኃላፊ
- ሻምበል ይኩኖአምላክ ተስፋዬ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በኮርፖሬት ማርኬቲንግና ሽያጭ የፕሮሞሽን ኃላፊ
- ኮሎኔል ደሴ ዘለቀ ብርሃን - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የአዳማ እርሻ ስራዎች ኢንዱስትሪ ስራ አስኪያጅ
- ሌተናል ኮሎኔል ሰለሞን በርሄ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በብረታ ብረት ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ የፋይናንስ ኃላፊ
- ሻለቃ ይርጋ አብርሃ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በህብረት ማሽን ቢዩልዲንግ ኢንዱስትሪ የፋይናንስ ኃላፊ
- ኮሎኔል ግርማይ ታረቀኝ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በኮርፖሬት ሎጂስቲክስና ሰፕላይ የንብረት አስተዳደር ኃላፊ
- ሻምበል ገብረስላሴ ገብረጊዮርጊስ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የኮርፖሬት ትራንስፎርሜሽን የአቅም ግንባታ ማዕከል ኃላፊ
- ሻምበል ሰለሞን አብርሃ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በኮርፖሬት ትራንስፎርሜሽን የስልጠና ኃላፊ
- ሻለቃ ጌታቸው ገብረ ስላሴ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የደን ምንጣሮ ክትትል ኃላፊ
- ሌተናል ኮሎኔል ይሰሃቅ ሀይለማሪያም አድሃኖም - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በኮርፖሬት ኮሜርሻልና ሲቪል ምርቶች ኦፕሬሽን የፕላኒንግና ኮንትሮል ኃላፊ
- ሻለቃ ክንደያ ግርማይ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የፋይናንስ ኃላፊ
- ሌተናል ኮሎኔል አዳነ አገርነው - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በኮርፖሬት ሎጂስቲክስና ሰፕላይ የንብረት ክፍል ኃላፊ
- ሻለቃ ጌታቸው አጽብሃ - በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ኢንፍራስትራክችርና ኮርፖሬሽን ማሽነሪ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኦፕሬሽን ኃላፊ
- ቸርነት ዳና - የዋይ ቲ ኦ ኩባንያ ባለቤትና ከብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን አመራሮች ጋር የጥቅም ትስስር የነበራቸው ደላላ
- አያልነሽ መኮንን አራጌ - ማስረጃ ልታጠፋ ስትል በቁጥጥር ስር የዋለች መሆናቸውን የፌዴራሉ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አስታውቋል።