የአማራ ክልል ከተሞች በመብራት ኃይል እጥረት ሳቢያ ከፍተኛ ችግር መሆናቸውን የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አስታወቀ - ኢዜአ አማርኛ
የአማራ ክልል ከተሞች በመብራት ኃይል እጥረት ሳቢያ ከፍተኛ ችግር መሆናቸውን የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አስታወቀ
አዲስ አበባ ህዳር 2/2011 በአማራ ክልል የሚገኙ ከተሞች የመብራት ኃይል እጥረት ሳቢያ ከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸውን የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አስታወቀ። የፌዴራል መንግስትም በክልሉ ያለው ኢ-ፍትሃዊ የመብራት አቅርቦች ችግር እንዲፈታ ጥሪ አቅርበዋል። የቢሮው ኃላፊ አቶ ፈንታ ደጀን ለኢዜአ እንዳስታወቁት፤ በክልሉ የሚገኙ ከተሞች በመብራት ኃይል አቅርቦትና እጥረት ምክንያት የሚፈለገውን ተግባር ማከናወን አልቻሉም። ባለፉት ዓመታት በክልሉ የሚገኙ ከተሞች ከሌሎች ክልሎች አንጻር ፍትሃዊ የኃይል ስርጭት እያገኙ እንዳልሆነ ገልጸዋል። ክልሉ በከተሞች ያለው የመብራት አቅርቦት እንዲስተካከል በተደጋጋሚ ጠይቋል ያሉት አቶ ፈንታ፤ የፌዴራል መንግስት ችግሩን እንዲፈታ ጠይቀዋል። የቢሮው ሃላፊ አሁን እየታየ ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል ስርጭትና አቅርቦት ችግር ሊፈታ እንደሚችል ያላቸውን እምነትም ገልጸዋል። የኤሌክትሪክ ኃይል ስርጭት ችግር በዘላቂነት መፍትሄ እንዲያገኝ ለማድረግ የማሰራጫ መስመሮችን ለማዘመን እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በቅርቡ ለኢዜአ መግለጹ ይታወሳል።