ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር ሆነው መመረጣቸው ለአህጉር ጥሩ ዜና ነው---የአፍሪካ ኀብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር - ኢዜአ አማርኛ
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር ሆነው መመረጣቸው ለአህጉር ጥሩ ዜና ነው---የአፍሪካ ኀብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር
አዲስ አበባ ጥቅምት 27/2011 ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር ሆነው መመረጣቸው ለአህጉር ጥሩ ዜና እንደሆነ የአፍሪካ ኀብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ተናገሩ። ሚስተር ፋኪ ዛሬ በብሔራዊ ቤተ መንግስት ከኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር በአህጉሪቱ ሰላምና ፀጥታ እንዲሁም አጀንዳ 2063 በተሰኘው የአፍሪካ ህብረት የልማት መርሃ ግብር ትግበራ ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል። ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ የአፍሪካ ኀብረትን በደንብ የሚያውቁ በመሆናቸው የአህጉሪቱን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ እንዲሁም አጀንዳ 2063ን ለማሳካት ድጋፍ እንደሚያደርጉ መናገራቸውን ሚስተር ፋኪ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ገልፀዋል። በሌላ በኩል ሊቀ መንበሩ ዛሬ ጠዋት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር በህዳር ወር 2018 በአዲስ አበባ የሚካሄደውን ልዩ የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔን በተመለከተ ምክክር አድርገዋል።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ጋር ባደረጉት በዚሁ ቆይታ በህብረቱ ሊካሄድ በታሰበው የማሻሻያ ፕሮጀክት ላይ የመከሩ ሲሆን ዶክተር አብይ ለፕሮጀክቱ ተፈጻሚነት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ መግለጻቸውን ሚስተር ፋኪ ተናግረዋል።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ጋር ባደረጉት በዚሁ ቆይታ በህብረቱ ሊካሄድ በታሰበው የማሻሻያ ፕሮጀክት ላይ የመከሩ ሲሆን ዶክተር አብይ ለፕሮጀክቱ ተፈጻሚነት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ መግለጻቸውን ሚስተር ፋኪ ተናግረዋል።