ጀግኒት የተሰኘው የማህበረሰብ ንቅናቄ መርሃ ግብር በይፋ ተጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
ጀግኒት የተሰኘው የማህበረሰብ ንቅናቄ መርሃ ግብር በይፋ ተጀመረ
አዲስ አበባ 26/2011 ጀግኒት የተሰኘው የማህበረሰብ ንቅናቄ መርሃ ግብር ዛሬ በአዲስ አበባ በይፋ ተጀመረ። የመርሃ ግብሩ ዓላማ የኢትዮጵያ ሴቶች ለአገር ልማትና ዕድገት ያላቸውን ሚና ለማጉላትና የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሴቶች ዕውቅና መስጠት ላይ ነው። በተለይም ሴት ልጅ “አትችልም” የሚለውን ስር የሰደደ ኋላ ቀር አመለካከት መለወጥና በሕብረተሰቡ ዘንድ የአስተሳሰብ ለውጥ የማምጣትን ግብ የያዘ ነው። 
በመርሃ ግብሩ ማብሰሪያ ላይ ፕሬዝዳንት ሳህለ ውርቅ ዘውዴ፣ ሚኒስትሮች፣ የክልል ፕሬዝዳንቶች፣ የምክር ቤት አፈ ጉባዔዎች፣ አርቲስቶችና ተዋቂ ግለሰቦች ተገኝተዋል። 'ጀግኒት' የተሰኘው ንቅናቄ “አለመች፣አቀደችና አሳካች” የሚሉትን መሪ ሐሳቦች የያዘ ሲሆን ሴት በሁሉም ዘርፍ ውጤታማና አሸናፊ ሆና እንድትወጣ የሚያነሳሳ ነው። መርሃ ግብሩ የፌደራል፣ የክልል፣ ዞንና ወረዳ ፣ የልማት ቡድኖችና ሌሎች አደረጃጀቶችን በመጠቀም ሚሊዮን ጀግኒትና ተተኪዎች የሚፈሩበት ንቅናቄ ነው።