በ2010 በጀት ዓመት በአትሌቲክስ ስፖርት ኦሮሚያ ክልልና የመከላከያ አትሌቲክስ ክለብ የተሻለ ነጥብ አስመዝግበዋል - ኢዜአ አማርኛ
በ2010 በጀት ዓመት በአትሌቲክስ ስፖርት ኦሮሚያ ክልልና የመከላከያ አትሌቲክስ ክለብ የተሻለ ነጥብ አስመዝግበዋል
አዲስ አበባ ጥቅምት 25/2011 በ2010 ዓ.ም በአትሌቲክስ ስፖርት የውጤት ደረጃ መሰረት በክልል ኦሮሚያ በክለብ ደግሞ የመከላከያ አትሌቲክስ ክለብ የተሻለ ነጥብ አስመዝግበዋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባለፈው የ 2010 ዓ.ም በአትሌቲክስ ስፖርት እንዳዝመስገቡት ውጤት ለክልሎችና ክለቦች ሽልማት አበርክቷል። ከክልሎች ኦሮሚያ ከሁሉም የተሻለ ነጥብ በማስምዝገብ የ240 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል። አማራ ክልል ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ የ180 ሺህ ብር የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶለታል። ደቡብ ክልልና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደግሞ ሁለቱም በእኩል ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቅ 140 ሺህ ብርና የትግራይ ክልል ደግሞ አምስተኛ ደረጃ በመያዝ የ80 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆነዋል። ሌሎች ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮችም እንደየደረጃቸው ተሸላሚ ሆነዋል። ከክለቦች መካከል ደግሞ የተሻለ ነጥብ ያስመዘገበው የመከላከያ አትሌቲክስ ስፖርት ክለብ ሲሆን የ300 ሺህ ብር የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶለታል። ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሁለተኛ በመሆን፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ የ240 ሺህ ብርና የ180 ሺህ ብር በተከታታይ ተሸላሚ ሆነዋል። ኦሮሚያ ስፖርት ክለብ፣ የፌደራል ማረሚያ፣ የፌደራል ፖሊስ፣ ሲዳማ ቡናና ጥሩነሽ ዲባባ ብሄራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ከአራተኛ እስከ ስምንተኛ ደረጃን እንደየቅደም ተከተላቸው ያጠናቀቁ ሲሆን የገንዘብ ሽልማትም ተበርክቶላቸዋል።