በአማራ ክልል በባህርዳርን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ሰልፍ እየተካሔደ ነው

ባህር ዳር ጥቅምት 18/2011 በአማራ ክልል በባህርዳር፣ በደሴ፣ ጎንደር፣ወልዲያና ደብረብርሃን ከተሞች በዛሬ ዕለት ሰልፍ እየተካሄደ ነው። የሰላማዊ ሰልፉ አላማ በጣና ሐይቅ ላይ በእንቦጭ አረም እየደረሰ ያለው ጥፋት ትኩረት እንዲያገኝና በላሊበላ ቅርሶች ላይ ለተጋረጠው አደጋ መፍትሔ እንዲሰጥበት ለሚመለከታቸው አካላት ለማመልከት ነው በደሴና ደብረብርሃን የሚካሄደው ሰልፍ ከተለያዩ አካባቢዎች በመነሳት ህዝቡ የተለያዩ መፈክሮች በማሰማት ወደ ሆጤና ደብረብርሃን ስታድየም አምርተዋል። የባህርዳርና የወልዲያ ህዝብም በዋና ዋና ጎዳናዎች በመዘዋዋር የተለያዩ መልዕክቶችን እያሰማ መሆኑ ታውቋል። የባህርዳርና የወልዲያ ህዝብም በዋና ዋና ጎዳናዎች በመዘዋዋር የተለያዩ መልዕክቶችን እያሰሙ መሆኑ ታውቋል። ከዚህ በተጨማሪም ከራያ አላማጣና ወልቃይት የማንነት ጥያቄዎች ጋር ተያይዞ እየታዩ ያሉ ግጭቶች ህጋዊ መንገድ እንዲፈቱ እንደሚፈልጉም በመልዕክቶቻቸው አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም