ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የሚመጡ አዲስና ነባር ተማሪዎችን ለመቀበል ተዘጋጅተናል - የከተማዋ ነዋሪዎች

70
ጅግጀጋ ጥቅምት 16/2011 ከተለያዩ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ወደ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የሚመጡ አዲስና ነባር ተማሪዎችን ለመቀበል መዘጋጀታቸውን አስተያየታቸውን የሰጡ የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ ለ2011 የትምህርት ዘመን ወደ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ለሚገቡ ተማሪዎች ቅበላን አስመልክቶ ዩኒቨርሲቲው ከባለድርሻ አካላት ጋር በክልል መስተዳደር ቅጥር ግቢ በሚገኘው ከሊ አደራሽ ትናንት ምክክር አካሄዷል፡፡ በምክክር መድረኩ ላይ ከከተማው 20 ቀበሌዎች የተውጣጡ የኃይማኖት አባቶች ፣ ሀገር ሽማግሌዎች፣ ጉሳ መሪዎች፣ ሴቶች፣ ወጣቶችና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ተሳትፈዋል፡፡ በክልሉ የሀገር ሽማግሌዎች ሸንጎ ሰብሳቢ ገራድ ኮልሚዬ ገራድ መሀመድ በዚሁ ጊዜ እንደገለፁት ወደ ተቋሙ የሚገቡ ተማሪዎችን በፍቅር ተቀብለው ለማስተናገድ ተዘጋጅተዋል፡፡ በከተማው ሐምሌ 28 ቀን 2010 የተከሰተው ችግር ከከተማው ህዝብ የመነጭ ባለመሆኑ በህብረተሰቡ ጥረት የሰላም ሁኔታው ወደ ነበረበት መመለሱን የገለፁት የሸንጎ ሰብሳቢው ተማሪዎች ያለምንም ስጋት መምጣት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ ሌላው ሼህ መሀመድ አህመድ በበኩላቸው ''ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ የሚገቡ ተማሪዎችን እንደ ልጆቻችን ተቀብለን ለማስተናገድና ትምህርታቸውን በሰላም እንዲከታተሉ ለማድረግ የሚጠበቅብኝን ሁሉ እወጣለሁ'' ብለዋል፡፡ ''ዩኒቨርሲቲው የእውቀት ማዕከል ብቻ በመሆኑ ተማሪዎች የፖለቲካ ዓለማ ለማራመድ ለሚፈልጉ ቡድኖች መጠቀሚያ እንዳይሆኑ መጠንቀቅ አባቸው'' ያሉት ደግሞ በኢትዮጱያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሶማሊ ሀገረ ስብከት ምትክል ስራ ኢስኪያጅ መጋቢ ምስጥር ናሆ ደረጀ ናቸው፡፡ ቤተ እምነቱ ወደ ዩኒቨርሲቲው ለሚመደቡ አዲስም ሆኑ ነባር ተማሪዎች ደማቅ አቀባበል ለማድረግ መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡ ''ተማሪዎች በትርፍ ጊዜያቸውም መልካም ስነ ምግባርን እንዲያዳብሩ ቤተክርስቲያኗ ታስተምራልች'' ብለዋል፡፡ የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳደር አቶ አደን ፋራህ የክልሉ መንግስት ወደ ጅግጅጋና ቀብር ደኃር ዩኒቨርሲቲዎች የሚመጡ ተማሪዎችን ለመቀበል ተዘጋጅበቷል፡፡ ጅግጅጋና ቀብር ደኃር ዩኒቨርሲቲዎች ለሚገቡ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በነፃነት እንዲማሩ የሚያስችላቸው አስተማማኝ ሰላም በክልሉ  ሁሉም አከባቢዎች በመኖሩ ወላጆች ያለምንም ስጋት ልጆቻቸውን እንዲልኩ ጥሪ አቀርበዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎቹ ከመማር ማስተማር ስራቸው በተጓዳኝ የአከባቢውን ማህበረሰብ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮችንለመፍታት የጥናትና ምርምር ስራዎችን በብዛትና በጥራት በማካሄድ ተልዕኮቸውን ለማሳካት ለሚያደርጉት ጥረት የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንትና የምርምርና አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኢልያስ ዑመር ዩኒቨርሲቲው ሦስት ሺህ አራት መቶ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ለመቀበል  ዝግጅት አጠናቋል፡፡ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ከክልሉ መንግስትና ህብረተሰብ ጋር በመተባበር ተማሪዎች ከጥቅምት 28 ጀምሮ አዲስ ተማሪዎች እንደሚቀብል ታውቀዋል፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም