በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት በመመረጣቸው ደስተኞች መሆናቸውን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ

194
አዲስ አበባ ጥቅምት 15/2011  ሳህለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸው በአገሪቱ የተጀመረው ለውጥ በሴቶች ላይ ያለውን ከፍተኛ መተማመን የሚያሳይ ነው ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ። አዲሷ ፕሬዝዳንት መንግስትና ህዝብ የጣሉባቸውን ኃላፊነት በመወጣት በአዲስ መንፈስ  ይተጋሉ የሚል ተስፋ እንዳለቸውም አስተያየት ሰጪዎቹ  ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ፕሬዚዳንት መሾማቸው፤ ስርዓቱ ሴቶች አገር መምራት እንደሚችሉ የሰጠውን እውቅና የሚያረጋግጥ ነው ሲሉም ተናግረዋል። ይህም አገር ተረካቢው ትውልዱን በተለይም ሴት ተማሪዎችንና ተማሪዎችና ወጣት ሴቶችን ለበለጠ ዓላማ ለማነሳሳት የሚያስችል አቅም እንደሚፈጥር ጠቅሰዋል። ከአስተያየት  ሰጪዎች መካከል አቶ ተክለ ወልድ  ጥላሁን ሴት ፕሬዝዳንት በመመረጡ  ለውጡ  ምን ያህል በሴቶች ላይ ያለውን  እምነት የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡ ለአገራችን  የመጀመሪያዋ  ሴት ፕሬዝዳንት በመሆናቸው  ለሌሎች ሴት እህትና እናቶች አርአያና ትምህርት ይሆናል ብዬ አስባለሁ ያሉት አቶ ጌታቸው  ሙንዬ  ናቸው፡፡ አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ የአገሪቱ ስድስተኛዋ ፕሬዚዳንት ሲሆኑ የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት ናቸው።        
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም