ኢትዮጵያ ሴት ፕሬዚዳንቷን በመሾም ታሪክ ሰራች - የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ሴት ፕሬዚዳንቷን በመሾም ታሪክ ሰራች - የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር
አዲስ አበባ ጥቅምት 15/2011 "ኢትዮጵያ ሴት ፕሬዚዳንቷን በመሾም ታሪክ ሰራች" አሉ የጥንታዊ ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን። የፕሬዝዳት ሳህለወርቅ ዘውዴ በዓለ ሲመትን የተከታተሉት የጥንታዊ ኢትዮጵያ ጀግኖች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን "ኢትዮጵያ ከባለፉት ስድስት ወራት ወዲህ በታሪክ ላይ ታሪክ እየሰራች ነው።" ብለዋል። የዶክተር አብይ አህመድ አዲሱ አስተዳደር የአገሪቱን የሴቶችን ካቤኔ አባላት ቁጥር ሀምሳ በመቶ ባደረገበት ማግስት ኢትዮጵያ ሴት ፕሬዚዳንቷን በመሾም ሌላ ታሪክ "እያስመዘገበች ነው" ይላሉ ልጅ ዳንኤል ጆቴ። የህዝብ ተወካዮችና የፌደሬሽን ምክር ቤቶች ዛሬ ባካሄዱት ልዩ የጋራ ስብሰባ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመን የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ተቀብለው በምትካቸው አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴን ሾመዋል።