ወደ አዳማ ከተማ ሊገባ የነበረ 17 ሽጉጦችና 45 ጥይቶች ተያዙ

66
አዳማ ጥቅምት 9/2011 በአሰላና በአዲስ አበባ መስመር ወደ አዳማ ከተማ ሊገባ የነበረ 17 ሽጉጥና 45 ጥይት ዛሬ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ የአዳማ ከተማ አስተዳደር ልዩ ዞን ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ዋና ሳጅን ወርቅነሽ ገልሜቻ እንደገለፁት ዛሬ ከጠዋቱ 1፡30 አካባቢ በአሰላ መስመር ወደ አዳማ መግቢያ ልዩ ስሙ ሶደሬ መንገድ ተብሎ በሚጠራው ቦታ በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ 2 ሹጉጦች ተይዘዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ከቀኑ 10 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ላይ ከአዲስ አበባ ቃሊቲ መነሃሪያ የተነሳው ኮድ 3 - 42617 ኦሮ  ሃይሩፍ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ አዳማ ከተማ መግቢያ ላይ ልዩ ስሙ መልከአዳማ በተባለው ስፍራ በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ ደግሞ 15 ሽጉጦችና 45 ጥይቶች ተይዘዋል፡፡ የጦር መሳሪያው ባለቤት ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ ህብረተሰቡ ተመሳሳይ ጥርጣሬ የሚያጭሩ የተለዩ ሁኔታዎች ሲያጋጥመው ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር ዋና ሳጅን ወርቅነሽ መልእክት አስተላለፈዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም