ቀጥታ፡

ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ዴንማርክ አቀኑ

አዲስ አበባ ጥቅምት 8/2011 ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ለይፋዊ የስራ ጉብኝትና በዓለም አቀፍ የአረንጓዴ ልማት ትብብር ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ ዴንማርክ ኮፐንሃገን ማቅናታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ። የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ለኢዜአ እንደገለጸው፤ ፕሬዚዳንቱ በዴንማርክ በሚኖራቸው ቆይታ ከአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሎክ ራሙሰን ጋር ተገናኝተው በሁለትዮሽ ሁለንተናዊ ግንኙነት ላይ ምክክር ያደርጋሉ። በተጨማሪም የተለያዩ አገሮች መሪዎች በሚሳተፉበት የዓለም አቀፍ የአረንጓዴ ልማት ትብብር ጉባኤ ላይ ተገኝተው ንግግር እንደሚያደርጉ ተጠቁሟል። ጉባኤው በዘርፉ የተመዘገቡ ውጤቶች እና የወደፊት አቅጣጫዎች ላይ ምክክር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። ኢትዮጵያና ዴንማርክ ከ20ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ቢሆንም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩት ግን በ1960ዎቹ ነው። ሁለቱ አገሮች በዘላቂ ግብርና፣ በስደተኞች ጉዳይ፣ በአየር ንብረት ለውጥ፣ ድህነትን በመዋጋት፣ በሰላምና ደህንነት እንዲሁም  በማህበራዊ ልማት ላይ ትብብር አላቸው። የኢትዮጵያ ዋነኛ የልማት አጋሮች መካከል ዴንማርክ ዋነኛዋ ስትሆን ከኢትዮጵያ ጋር የልማት ትብብር የጀመረቸው እ.አ.አ በ2004 ነው።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም