ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋን ሴት የአገር መከላከያ ሚኒስትር ሾመች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋን ሴት የአገር መከላከያ ሚኒስትር ሾመች
አዲስ አበባ ጥቅምት 6/2011 ኢንጂነር አይሻ መሃመድ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያዋ የአገር መከላከያ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ሰብሰባ ኢንጂነር አይሻ መሃመድን የአገር የመከላከያ ሚኒስትር አድርጓቸዋል። ኢንጂነር አይሻ የአፋር ክልል ተወላጅ ሲሆኑ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በሲቪል ኢንጂነሪንግ፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በትራንስፎርሜሽናል ሊደር ሺፕ ኤንድ ቼንጅ አግኝተዋል። በአፋር ክልል የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ቢሮ ሃላፊ በመሆን ያገለገሉ ሲሆን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትርም ነበሩ። በአሁኑ ወቅትም የኮንስትራክሽን ሚኒስትር ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ። በዛሬው የምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባም የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሴት የአገር መከላከያ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል። ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከተሾሙት 20 የካቢኔ አባላት መካከል አስሩ ሴቶች ናቸው።