የአምስት የፌዴራል ተቋማት ተጠሪነት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚሆን ይጠበቃል - ኢዜአ አማርኛ
የአምስት የፌዴራል ተቋማት ተጠሪነት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚሆን ይጠበቃል
አዲስ አበባ ጥቀምት 6/2011 በመካሄድ ላይ ያለው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ መደበኛ ስብሰባ የአምስት የፌዴራል ተቋማትን ተጠሪነት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚያደርግ ይጠበቃል። እነዚህ ተቋማት የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ኤጀንሲ፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን እንዲሁም የፌዴራል የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ናቸው። ውሳኔው ተቀራራቢ ተልዕኮ ያላቸውን ተቋማት ውጤታማና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ በማሰባሰብ እንደገና የማዋቀሩ ተግባር አካል ነው።