ቀጥታ፡

በትግራይ ክልል 11ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ነገ ይከበራል

መቀሌ ጥቅምት 4/2011 በትግራይ ክልል 11ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ነገ እንደሚከበር የክልሉ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ገለጸ። የጽህፈት ቤቱ የህዝብ ግንኙነትና የኮንፈረንስ አገልግሎት የሥራ ሂደት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ታረቀ ቀኑን በሰላማዊ ሰልፍና በፓናል ውይይት ለማክበር ዝግጅቱ መጠናቀቁን አስታውቀዋል፡፡ የክልሉ ሁሉም ከተሞች ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣት ለሰንደቅ ዓላማቸው ያላቸውን ክብር በመግለጽ ያከብሩታል ብለዋል፡፡ ዕለቱ ዜጎች ለሰንደቅ ዓላማው ያላቸውን ክብርና የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች አንድነት የሚንጸባርቅበት እንደሚሆንም ገልጸዋል፡፡ ከጠዋቱ  4 ሰዓት ከ30 ላይ የሰንደቅ ዓላማ የመስቀል ሥነ ሥርዓት እንደሚካሄድም አቶ ሙሉጌታ አስታውቀዋል። 'የዘንድሮው የሰንደቅ ዓላማ ቀን የሚከበረው ''ሰንደቅ ዓላማችን ለዴሞክራሲያዊ አንድታችን መሠረት ነው!'' በሚል መሪ ቃል ነው።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም