ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን እንዲመሩ በድጋሚ ተመረጡ - ኢዜአ አማርኛ
ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን እንዲመሩ በድጋሚ ተመረጡ
አዲስ አበባ ጥቅምት 4/2011 ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ትተውት የነበረውን የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ በፕሬዚዳንትንት ለመምራት በድጋሚ ተመረጡ። የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን 16ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄዷል። የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴን በፕሬዚዳንትነት እየመሩ የሚገኙት ዶክተር አሸብር ባለፈው ዓመት በተካሄደው የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለመሳተፍ ሲሉ ሲመሩት የነበረውን ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽንን መልቀቃቸው ይታወቃል። በወቅቱ ከቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ኃላፊነታቸው የለቀቁትም በአንድ ጊዜ ሁለት የስፖርት ፌዴሬሽኖችን መምራት የማይቻል መሆኑን ተከትሎ ነው። ከዶክተር አሸብር በተጨማሪ ፌዴሬሽኑ በትናንትናው ጠቅላላ ጉባኤው በምክትል ፕሬዚዳንትነት አቶ ጌቱ ኢሳያስን ሲመርጥ ሌሎች ሰባት ሰዎችን ደግሞ በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴነት መርጧል ። በዚህ ጉባኤ በቀጣይ የባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና በሰፊው ሊሰራ እንደሚገባም ተመላክቷል። ከዚህ በተጫማሪ በኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ውስጥ የሴቶችን ተሳታፎም ማሳደግ እንደሚገባ ተገልጿል።