ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ ጥቅምት 4/2011 የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብተዋል። ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት እንደሚኖራቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ ለኢዜአ ተናግረዋል። ፕሬዚዳንቱ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።