ቀጥታ፡

በሃዋሳ ከተማ ዛሬ ምሽት በተከሰተ የእሳት ቃጠሎ ጉዳት ደረሰ

ሀዋሳ መስከረም 29/2011 ዛሬ ምሽት በሃዋሳ ከተማ ልዩ ስሙ አሮጌ ገበያ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ መከሰቱን የከተማው ፖሊስ አስታወቀ። የተነሳውን የእሳት ቃጠሎ ለመቆጣጠር ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ነው ፖሊስ  የገለጸው፡፡ የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር መስፍን ዴቢሳ ለኢዜአ እንደገለጹት ፖሊስ ቃጠሎውን ለመቆጣጠር ከሃዋሳ ከተማ የእሳት አደጋ መከላከል ግብረ-ኃይል ጋር በመሆን እየሰራ ይገኛል። የቃጠሎው መንስኤ ለጊዜው እንዳልታወቀ የተናገሩት የፖሊስ አዛዡ ይህ ዜና እስከተሰራበት ሰዓት ድረስም በቁጥጥር ስር እንዳልዋለ አመልክተዋል። የደረሰው የእሳት አደጋ ያስከተለው የጉዳት መጠንም በቀጣይ ተጣርቶ እንደሚገለጽ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም