ቀጥታ፡

በምስራቅ አፍሪካ የታዳጊዎች የእጅ ኳስ ውድድር የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ሁለተኛ ደረጃ ይዞ አጠናቀቀ

አዲስ አበባ ግንቦት 12/2010 በምስራቅ አፍሪካ የዞን አምስት የታዳጊዎች የእጅ ኳስ ውድድር ኢትዮጵያን የወከለው ከ18 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቋል። የዓለም አቀፉ የእጅ ኳስ ፌዴሬሽን በኡጋንዳ ርዕሰ መዲና ካምፓላ ከግንቦት 6 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው ውድድር ዛሬ ፍጻሜውን አግኝቷል። የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከኬንያ አቻው ጋር ባደረገው ጨዋታ 23 ለ 17 በሆነ ውጤት ተሸንፏል። በዚህም መሰረት ኬንያ የወርቅ ሜዳሊያና የዋንጫ ተሸላሚ ስትሆን ኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያና ዋንጫ ማግኘቷን ከኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል። አዘጋጇ ኡጋንዳ ከ18 ዓመት በታች የእድሜ ዘርፍ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ባደረገው የደረጃ ጨዋታ የኬንያ አቻውን 29 ለ 23 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል። ለፍጻሜ በተደረገ ጨዋታ ሩዋንዳ አዘጋጇ አገር ኡጋንዳን አሸንፋ ከ20 ዓመት በታች የእድሜ ዘርፍ  አሸናፊ ሆናለች። -  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም