በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን 127ኛውን የአድዋ ድል በዓል አከበሩ - ኢዜአ አማርኛ
በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን 127ኛውን የአድዋ ድል በዓል አከበሩ
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 23/2015 በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን 127ኛውን የአድዋ ድል በዓል አክብረዋል።
በዓሉን በእንግሊዝ፣ በጣልያን፣ በፈረንሳይ፣ በግሪክ፣ በካናዳ እና በደቡብ አፍሪካ መከበሩ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መረጃ በአሜሪካም ከሰአታት በኋላ በዓሉ እንደሚከበር ገልጿል።
በተጨማሪም በጃፓን፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ በኳታር፣ በቤይሩት እና በዩጋንዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዓሉን ማክበራቸው ተመልክቷል።
127ኛው የአድዋ ድል በዓል በኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።