ቀጥታ፡

127ኛው የአድዋ ድል በዓል በሲዳማ ክልል እየተከበረ ነው

ሐዋሳ (ኢዜአ) የካቲት 23/2015 127ኛው የአድዋ ድል በዓል በሲዳማ ክልል “አድዋ የአንድነት፣ ጀግንነትና ጽናት” በሚል መሪ ሃሳብ በሐዋሳ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።

በበዓሉ ላይ በብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ: የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ጸጋዬ ቱኬን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የአገር መከላከያ ሰራዊት እና የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አመራሮች፣አባት አርበኞች እና የተለያዩ ሕብረተሰብ ተወካዮች ታድመዋል ።

የአድዋ ድል በዓል በኪነ ጥበብ ዝግጅቶች እና ፓናል ውይይት በመከበር ላይ ይገኛል።

በመርሐግብሩ የአድዋን ድል የተመለከተ የመነሻ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።

የአድዋ ድል በዓል የውጭ ወራሪ የነበረው የጣሊያን ጦር ድባቅ ተመቶ እና ሽንፈትን ተከናንቦ የተመለሰበት፤ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካዊያንም ታላቅ ድል እንደሆነ ይገለጻል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም