ቀጥታ፡

የአድዋ በዓል በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተከበረ ነው

የካቲት 23 ቀን 2015 (ኢዜአ) ፡- 127ኛው የአድዋ በዓል በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች እየተከበረ ነው።

የ"አድዋ ድል አንድነት፣ ጀግንነትና ፅናት "በሚል መሪ ሃሳብ እየተከበረ ያለው በዓሉ በሰላማዊ ሰልፍ፣ በፓናል ውይይትና በሌሎችም ዝግጅቶች መሆኑን በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙ የኢዜአ ሪፖርተሮች እየዘገቡ ነው።

በዓሉ እየተከበረባቸው ካሉ የሀገሪቱ አካባቢዎች መካከል አሶሳ፣ ጋምቤላ፣ ድሬዳዋ፣ ፣ ባህርዳር ፣ ጎንደርና ደብረ ብርሃን ይገኙበታል ።

የድሬዳዋ ሪፖርተራችን እንደዘገበው፤ የኢትዮጵያዊያንን ህብረ ብሔራዊ የድል መገለጫ የሆነው የአድዋ በዓል በደመቀ ስነ-ስርዓትበታሪካዊው የድሬደዋ ምድር ባቡር አደባባይ በሰልፍና የድሉን ፍሬዎች በሚዘክሩ መልዕክቶች እየተከበረ ነው።

በአከባበሩ ስነስርዓት ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ፈትሂያ አደን፣ ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ ና የካቢኔ አባላት፣ የፌደራልና የድሬዳዋ ፖሊስ ፣ የመከላከያና የአየር ኃይል አመራሮችና አባላት እንዲሁም በየደረጃው የሚገኘው የህብረተሰብ ክፍል እየተሳተፉ ነው።

የበዓሉ ተሳታፊዎች ድሉ ለቀጣይ ህብረ ብሔራዊ አንድነትና ፅናት ስንቅ በመሆኑ ይህንን በመላበስ ለሀገር ዘላቂ ሰላምና ለብልፅግና መረጋገጥ የድርሻቸውን እንደሚወጡ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም