ቀጥታ፡

የአድዋ ድል በዓል ለኢትዮጵያውያን የአንድነት እና የነጻነት ምልክት ነው--አምባሳደር ዣኦ ዢዩዋን

አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 23/2015 “የአድዋ ድል በዓል የኢትዮጵያውያን አንድነት እና የነጻነት ምልክት ነው” ሲሉ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዢዩዋን ገለጹ።

127ኛው የአድዋ ድል በዓል በመላው ኢትዮጵያውያን ዘንድ በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ነው።

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዢዩዋን “የጥቁር ሕዝብ የነጻነት ድል የኢትዮጵያውያን የአንድነት አርማ ደማቅ ታሪክ አድዋ፤ እንኳን ለ127ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ” ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ ገልጸዋል።

“የአድዋ ድል በዓል የኢትዮጵያ ሕዝብ የአንድነት እና የነጻነት ምልክት ነው” ሲሉም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም