ቀጥታ፡

የዓድዋ ድል የኢትዮጵያና ሩስያን ግንኙነት በጽኑ መሠረት ላይ ያቆመ ታሪካዊ ሁነት ነው- አምባሳደር ኢቭጌኒ ተረክሂን

የካቲት 23/2015 (ኢዜአ) የዓድዋ ድል የኢትዮጵያንና ሩስያን ግንኙነት በጽኑ መሠረት ላይ ካቆሙ ታሪካዊ ሁነቶች አንዱ ነው ሲሉ በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተረክሂን ገለጹ።

በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢቭግኒ ተርክሂን 127ኛውን የአድዋ ድል በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አምባሳደሩ በመልዕክታቸው የአድዋ ድል የቀኝ ገዥነትን አስተሳሰብና አላማ በመስበር የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካውያን የድል ምልክት ሆኗል ብለዋል።

የዓድዋ ድል የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጀግንነት፣ ወኔ፣ ጥንካሬና አንድነት ማሳያ ነው ሲሉም አውስተው “አድዋ አይበገሬ በሚል የሚታሰበውን የቀኝ ገዥነት አስተሳሰብ በመገርሰስ ከቀኝ ግዛት ለመውጣት ለሚታገሉ አፍሪካውያን የብርታት ምንጭ እንዲሁም አብሪ ኮኮብ ሆኖ ያገለገለ ታላቅ ድል ነው” በማለት ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተሰሚነት በማጉላትና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን በማጠንከርም አድዋ ሚናው የጎላ ነው ሲሉ ያስገነዘቡት አምባሳደሩ ለፓን አፍሪካኒዝም መጠንሰስም መነሻ መሆኑን ተናግረዋል።

በአድዋል ድል በኒኮላይ ሊኦኔቴቭ የተመራ የሩስያ በጎ ፍቃደኞች ቡድን እንደተሳተፈ ያነሱት አምባሳደር ኢቭግኒ ተርክሂን ልዑኩ በህክምና አቅርቦት፣ በጦር ድጋፍና በሌሎችም ጉዳዮች ኢትዮጵያን ደግፎ በጦርነቱ መሳተፉን አብራርተዋል።

ከጦርነቱ ማብቃት ሁለት ዓመታት ኋላ የሁለቱ ሀገራት ዘመናዊ የዲፕሎማሲ ግንኙነት መጀመሩን ተናግረው የዓድዋ ድል የኢትዮጵያንና ሩስያን ግንኙነት በጽኑ መሠረት ላይ ካጸኑ ታሪካዊ ሁነቶች አንዱ ነው ሲሉ አስታውቀዋል።

የዓድዋ ድል ከጦርነትም ድል በላይ የሀገር ወዳድነት፣ የአልሸነፍም ባይነትና በአንድነት ለአላማ የመቆምን ታላቅነት ያሳያ አሻራ ነው በማለትም አምባሳደሩ የመልካም በዓል ምኞታቸውን አጠቃለዋል።

የዓድዋ ድል የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጀግንነት፣ ወኔ፣ ጥንካሬና አንድነት ማሳያ ነው ሲሉም አውስተው “አድዋ አይበገሬ በሚል የሚታሰበውን የቀኝ ገዥነት አስተሳሰብ በመገርሰስ ከቀኝ ግዛት ለመጣት ለሚታገሉ አፍሪካውያን የብርታት ምንጭ እንዲሁም አብሪ ኮኮብ ሆኖ ያገለገለ ታላቅ ድል ነው” በማለት ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተሰሚነት በማጉላትና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን በማጠንከርም አድዋ ሚናው የጎላ ነው ሲሉ ያስገነዘቡት አምባሳደሩ ለፓን አፍሪካኒዝም መጠንሰስም መነሻ መሆኑን ተናግረዋል።

በአድዋል ድል በኒኮላይ ሊኦኔቴቭ የተመራ የሩስያ በጎ ፍቃደኞች ቡድን እንደተሳተፈ ያነሱት አምባሳደር ኢቭግኒ ተርክሂን ልዑኩ በህክምና አቅርቦት፣ በጦር ድጋፍና በሌሎችም ጉዳዮች ኢትዮጵያን ደግፎ በጦርነቱ መሳተፉን አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም