127ኛው የአድዋ ድል በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
127ኛው የአድዋ ድል በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 23/2015 127ኛው የአድዋ ድል በዓል በምንሊክ አደባባይ፣ በአደዋ ድልድይና መስቀል አደባባይ በተለያዩ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ይገኛል።
የፌዴራል ፖሊስ ማርች ባንድ ልዩ ልዩ ሕብረ ዝማሬዎችን እያሰማ ነው።
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት አመራሮች በዓሉን ምክንያት በማድረግ የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።
በስነ-ስርዓቱ ላይ የመከላከያ ሚኒስቴር ተወካይ ሌተናል ጀነራል ዓለምእሸት ደግፌ፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ በምኒልክ አደባባይ የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።