ቀጥታ፡

የኢፌዴሪ አየር ሃይል በቦረና ዞን በድርቁ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የምግብ ቁሳቁስ እና የእንስሳት መኖ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ(ኢዜአ) የካቲት 22/2015 የኢፌዴሪ አየር ሃይል በቦረና ዞን በድርቁ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የምግብ ቁሳቁስ እና የእንስሳት መኖ ድጋፍ አደረገ፡፡

ድጋፉን የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ በተገኙበት ለዞኑ የአገር ሽማግሌዎች እና የስራ ኃላፊዎች አስረክበዋል።

የአየር ኃይል የሰራዊት አባላት በራሳቸው ተነሳሽነት ድጋፉን ማሰባሰባቸውንና ለእንስሳት መኖነት በአየር ኃይሉ ግቢ ውስጥ የተመረተ መሆኑን ሌተናል ጄኔራል ይልማ ገልጸዋል።

ከመኖው በተጨማሪ ስንዴ እንዲሁም የእንስሳት ምግብ እንደሚገኝበት እና በቀጣይ አየር ኃይሉ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖችን የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም