ቀጥታ፡

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ(ኢዜአ) የካቲት 21/2015 በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት መርሐግብር ተራዝመው ከነበሩ ጨዋታዎች መካከል ዛሬ ሁለቱ ይከናወናሉ።

በድሬዳዋ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት የድሬዳዋ ስታዲየም ምቹ ባለመሆኑ አራት ጨዋታዎች መራዘማቸው አይዘነጋም።

የፕሪሚየር ሊጉ አክሲዮን ማህበር የውድድር እና ስነ ስርዓት ኮሚቴ ጨዋታዎቹ ዛሬ እና ነገ እንዲካሄዱ መወሰኑ ይታወቃል።

በዚሁ መሰረት ዛሬ ሲዳማ ቡና ከኢትዮ ኤሌትሪክ (ከተቋረጠበት 18ኛው ደቂቃ የሚቀጥል) ከቀኑ 10 ሰአት እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና ከፋሲል ከነማ ከምሽቱ 1 ሰአት በድሬዳዋ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ነገ ከቀኑ 10 ሰአት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከድሬዳዋ ከተማ፤ ባህር ዳር ከተማ ከወላይታ ዲቻ ከምሽቱ 1 ሰአት ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም