በገንዘብ ሚኒስቴር አቶ አህመድ ሺዴ የተመራው የልዑካን ቡድን በአሊባባ ግሩፕ ኩባንያ ጉብኝት አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
በገንዘብ ሚኒስቴር አቶ አህመድ ሺዴ የተመራው የልዑካን ቡድን በአሊባባ ግሩፕ ኩባንያ ጉብኝት አደረገ
አዲስ አበባ(ኢዜአ) የካቲት 21/2015 የገንዘብ ሚኒስቴር አቶ አህመድ ሺዴ የተመራው የልዑካን ቡድን በቤጂንግ የሚገኘው የአሊባባ ግሩፕ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ዋና መቀመጫ ጉብኝት አደረገ ።
ሚኒስትሩ ከኩባንያው ምክትል ፕሬዝዳንት ሊዩ ናን ጋርም ተወያይተዋል።
ልዑካን ቡድኑ የኩባንያውን ታሪክ፣ እድገት እና ቀጣይ እቅዶችን አቅፎ የያዘውን መሰብሰቢያ አዳራሽ ጎብኝቷል።
ከአሊባባ ግሩፕ አመራሮች ጋር ኢትዮጵያ እና ኩባንያው በኢ-ኮሜርስ እና በዲጂታል ኢኮኖሚ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ፍሬያማ ውይይት መካሄዱን በቤጂንግ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።